top of page
ዘረኝነት በዚህ ያብቃ !

የፕሮጀክት፦ክትትል ዘረኝነትን ለመዋጋት የፓልመርሪፖርት ምክሮችና ሃሳቦች ፤ 

CC BY-SA 4.0: dujerit

ኮሚቴው  መከረ፤ መንግስት አጸደቀ በተግባርስ ምን እየተደረገ ነው ?​

በ2015 ዓ.ም ወጣት ኢትዮጵያውያን በደልና ዘረኝነት በዛብን ብለው የተለያዩ ሰላማዊ ሰልፎችን 
በማዘጋጀት ድምጻቸውን አሰሙ ። ለዚህ መነሻ የሆናቸውም ለረዥም  ጊዜ እየተፈጸመ የቀጠለውን በደልና መሳናክሎች ስለመረራቸው ነበር ፡፡  በተለያዩ ቦታዎች  በስራ ቦታዎች፤  በትምህርት ተቋማት ፤ ህግ በተዛባ መልኩ በተሰጡ ፍርዶች ቁጥራቸው ከህብረተሰቡ ቁጥር አንጻር ብዙ የሆኑ ወጣቶች ለእስር ተዳርገዋል  ፡፡ 
በዚህ ምክንያት ዘረኝነትን ለመዋጋት የተለያዩ መ/ቤቶች ባለሙያዎችን ያካተተ ተቋም እንዲመሰረት ተወሰነ ፡፡
በሐምሌ 2016 ዓ.ም በፍትህ ሚኒስትር ስራ አስኪያጅ ስም የተሰየመው የፓልመር ኮሚቴ ሪፖርቱን አቀረበ  የተወሰኑ ሃሳቦችም በመንግስት ውሳኔዎች ተስተካክለው ነበር ።
ከቀረበው ሪፖርት አንደኛው ውሳኔም  በመንግስት ቁጥጥር ስር የሆነ ዘረኝነትና አድልዎን የሚዋጋና ቢሮክራሲን የሚያስወግድ ሁሉም በእኩልነት መንገድ የሚያስተናግዱበት መንገዶች እንዲያመቻች በማቀድ ነው ።
ምንም እንኳን  ይህ ሪፖርት መነሻውና ትኩረት ያደረገው በኢትዮጵያ ይሁዳውያን  ችግር ላይ ቢሆንም ሌሎች የእስራኤል ህብረተሰብ ክፍሎች ማለትም  እንደ አረቦች ፤ከአረብ ሀገራት የመጡ ይሁዲዎች  ፤ሌዚቢያን ፤ጌዎች አካለ ስንኩላን ፤ ማየት የተሳናቸውን በስደት ወደ እስራኤል የገቡ የሌላ ሀገር ዜጎች ላይ የሚከሰቱ ጉዳዮችንም ያካትታል ። በተለያዩ ቦታዎች ማለትም በየመስሪያ ቤቱ በየትምህርት  ተቋማት ፤ የሚከሰቱ መሰናክሎች ኋላ ቀር አመለካከቶች፤ ጥላቻወችን ከወዲሁ ለመቅረፍ እንዲረዳ የታቀደ ነው ፡ ስለዚህ  የፓልመር ኮሚቴ የሰጠው  ሃሳብ በእነርሱም  ተፈጻሚነት ይኖረዋል ማለት ነው ።
 የዜጎች መብት አስከባሪና ተቆርቋሪ ድርጅት ከዜጎች እውቀት ማጎልመሻ ድርጅትና የዜጎችን አቅም ማዳበሪያ ማሰልጠኛ ማእከል ተቋማት ጋር በመተባበር የፓልመር ሪፖርት ያቀረበውን 16 ሃሳቦች ይፈትሻል ይከታተላል ። በስራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል ።
እኛም እነዚህ የመረጥናቸው  16 ሃሳቦች  በህብረተሰባችን ውስጥ ዘረኝነትና አድልዎ እንዳይስፋፋና እንዳይቀጥል ምክንያት ሆነው ስላገኘናቸው ነው ።
እነዚህ ሃሳብና አስተያየቶች ስራ ላይ ከዋሉ በሀገራችን ተንሰራርቶ የሚገኘው ዘረኝነትና አድልዎን  ለመቅረፍ በጣም ይረዳሉ ብለን እንገምታለን ።
እኛም በዚህ ድህረ ገጽ የቀረቡትን ሃሳቦች ፤ የተወሰኑ ውሳኔዎች ተግባራዊ መሆናቸውን ዘረኝነትንና አድሎን ለማስወገድ የተደረጉ እንቅስቃሴዎችን እናቀርባለን  ። ድህረ ገጹምቀጣይነት ባለው መንገድ ወቅታዊ ዜናዎችን ያቀርባል ፦ የቀረበውን የምክር ሃሳብ ለመመልከት ምስሉን ይጫኑ ! 

Amharic-recs

የዜጎች መብት ተቆርቋሪና አስከባሪ ድርጅት ዘረኝነትና አድሎን ለመታገል ያደረጉትን የስራ እንቅስቃሴ በተመለከተ እዚህ ላይ ይጫኑ ! ( እብራይስጥ )

ዘረኝነትን በተመለከተ ለሚቀርቡ ትምህርታዊ መረጃዎች እዚህ ላይ ይጫኑ ! (እብራይስጥ )

አድሎና በደል ደርሶብዎታል ? የዜጎች መብት ተቆርቋሪና አስከባሪ ድርጅት ሰራተኞች ጋር አቤቱታ ያሰሙ !

Photos: Dreamstime.com, © Rafael Ben Ari | Dreamstime.com, Keren Manor, Activestills, © Fotokon | Dreamstime.com

bottom of page